094 046 4646/0940 565656    
info@sainturaelclinic.com
Follow Us:

View Blog

ኦቾሎኒ

ኦቾሎኒ እንደ ባቄላ፣ አተርና አኩሪ አተር ከአበባ እህሎች ዉስጥ የሚመደብ ሲሆን በፕሮቲን፣ ስብና በተለያዩ ጤናማ ንጥረ ነገሮች የበለፀገ ነው።

ኦቾሎኒ በጤናማ ስብና ከፍተኛ ጥራት ባለው ፕሮቲን የተሞላ ነው። እንዲሁም በካሎሪ ይዘቱ ከፍ ያለ ነዉ። ስለሆነም በመቶ ግራም ኦቾሎኒ ዉስጥ 567 ግራም ካሎሪ፣25.8 ግራም ፕሮቲን፣49.2 ግራም ስብ፣ 16.1 ጋርቦድራትና ሌሎች ንጠረነገሮች በብዛት ይገኛሉ።

ኦቾሎኒ ከፍተኛ ስብ  ይይዛል ይህም በአብዛኛው ሞኖና ፖሊዩሳቹሬትድ ፋቲ አሲዶችን ያካተተ ሲሆን ይህም  ብዙውን ጊዜ የኦቾሎኒ ዘይት ለመሥራት ያገለግላሉ

አንዳንድ ሰዎች ለኦቾሎኒ ፕሮቲኖች አለርጂ ቢኖራቸዉም ከእፅዎቶች ከሚከኝ ፕሮቲን ኦቾሎኒ ለየት ያለ ጥሩ የፕሮቲን ምንጭ ነው

ኦቾሎኒ  የተለያዩ የቪታሚኖች እና ማዕድናት ምንጭ ሲሆን ከነዚህም ዉስጥ

·         ባዮቲን፦ ኦቾሎኒ በእርግዝና ወቅት ጠቃሚ የሆነው የባዮቲን ከፍተኛ ምንጭ ነዉ። የፎሌት፦  ፎሌት ብዙ ጠቃሚ ተግባራት ያሉት ሲሆን በተለይም በእርግዝና ወቅት አስፈላጊ ነው ።

·         ቫይታሚን ኢ፦ ቫይታሚን ኢ ጠንካራ አንቲኦክሲዳንት ሲሆን በስብ ምግቦች ዉስጥ በብዛት ይገኛል

·         ኒያሲን፦ ወይም ቫይታሚን ቢ 3 ምንጭ ሲሆን የልብ ህመምን ጨምሮ ሌሎች ህመሞችን ለመከላከል ይረዳል።

·         በተጨማሪም ኦቾሎኒ የመዳብ፣ የማንጋኔዝ፣ የቲያሚንና  የፎስፈርስ ምንጭ ነዉ።

ለልብ   ጤንነት

ኦቾሎኒ ጤናማ የስብ አይነቶች የሆኑ አንደሳቹሬትድ ፋቲ አሲድን በከፍተኛ መጠን የያዘ ሲሆን  የኮሌስትሮል መጠንን በመቀነስ የልብ ህመምን ይከላከላል። እንዲሁም ትናንሽ የደም መርጋት እንዳይፈጠር በመከላከል የልብ ድካምና በስትሮክ በሽታ የመያዝ እድልን ይቀንሳሉ።

ክብዳት ለመቀነስ

 ብዙ ፕሮቲን ያላቸው ምግቦች ባነሰ ካሎሪ የጥጋብ ስሜት እንዲሰማዎት ሊረዱዎት ይችላሉ። ይህም የሰዉነትዎን ክብደት ለመቀነስ ይረዳል።

የስኳር ችግርን ለመቀነስ ይረዳል

ኦቾሎኒ አነስተኛ የስኳር መጠን ያለዉ ሲሆን ቢመገቡት የደም የስኳር መጠንዎን አይጨምርም። ጥናቶች እንደሚያሳዩት ኦቾሎኒን መመገብ ሴቶች አይነት 2 የስኳር ተጋላጭነታቸዉን ይቀንሳል።

የሰዉነት መቆጣትን  ይቀንሳል  

ኦቾሎኒ ጥሩ የፋይበር ምንጭ ሲሆን ይህም በሰውነትዎ ውስጥ መቆታትን ለመቀነስና ለምግብ መፍጫ ስርዓትዎ ይረዳል።

ካንሰርን ለመከላከል

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ለአረጋውያን የኦቾሎኒ መመገብ በጨጓራ ካንሰር የመያዝ እድልን ይቀንሳል።



Share with: