የድድ መድማትን ለመከላከል የሚከተሉትን ነገሮች ይተግብሩ
1. የአፍዎንና የጥርስዎን ጤንነት መጠበቅ
የድድ መድማት የአፍ ጤንነትን ካለመጠበቅ ሊከሰት ይችላል። በድዱ ላይ የሚጋገሩ ( ፕሌክ) ነገሮች ካሉ ድድዎ ሊቆጣና ሊደማ ይችላል። የአፍዎነና ጥርስዎን ጤንነት ለመጠበቅ በቀን ቢያንስ ሁለት ጊዜ ጥርስዎን ይቦርሹ።
2. ማጨስ ያቁሙ፦ ከልብ ህመም፣ ከሳንባ ካንሰርና ስትሮክ በተጨማሪ ሲጋራ ማጨስ ከድድ ህመም ጋርም ይገኛናል። ሲጋራ ማጨስ ከፍተኛ የድድ ህመም ሊያማጡ ከሚችሉ ነገሮች ዉስጥ አንዱ ነዉ። ማጨስን ማቆም ድድዎ ቁስለት ካለዉ እንዲድንና መድማቱ እንዲያቆም ይረዳል።
3. የቫይታሚን ሲ አጠቃቀምን ይጨምሩ፦ በቫይታሚን ሲ የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ የሰውነትን በሽታ የመከላከል ስርዓትን በማጎልበት የድድ መድማትን የሚያስከትሉ የድድ ኢንፌክሽኖችን ለመከላከል ይረዳል። ስለሆንም በቫይታሚን ሲ የበለፀጉ ምግቦችን እንደ ብርቱካን፣ስኳር ድንች፣ካሮትና የመሳሰሉትን መመገብ ያስፈልጋል።
4. በምግብዎ ዉስጥ የቫይታሚን ኬ መጠን ይጨምሩ፦ ቫይታሚን ኬ ደምዎ እንዲረጋ ስለሚረዳ ጠቃሚ ንጥረ ነገር ነው። የቫይታሚን ኬ ዕጥረት ካለዎ ድድዎ በቀላሉ የመድማት ችግር ያመጣል። ስለሆነም በፋይታሚ ኬ የበለፀጉ ምግቦችን እንደ ቆስጣ፣ ሰላጣ፣ ያበባ ጎመን፣ሙስታርድ ግሪንና የመሳሰሉትን ይመገቡ
5. ቀዝቃዛ ነገር ይያዙበት፦ የድድ መድማቱ በአደጋ ምክንያት የተከሰት ከሆነ አሊያም ዕብጠትና መቆጣት ነገር ካለዉ ቀዝቃዛ ነገር ይያዙበት።
6. የሚመገቡትን የካርቦሀይድሬት መጠን ይቀንሱ፦ የካርቦሃይድሬት መጠንን መቀነስ የድድ ጤናን በማሻሻል የድድ በሽታን ለመከላከል ይረዳል።ካርቦሃይድሬትስና ስኳር የበዛባቸው ምግቦች በድድ ላይ ቆሻሻ አንዲጋገር(ፕሌክ)ና የባክቴሪያዎችን እድገት ያበረታታሉ
7. በጨዋማ ዉሃ አፍን መጉመጥመጥ፦ ባክቴሪያና የድድ መቆጣት የድድ በሽታን ስለሚያስከትል አዘውትሮ አፍዎን በሞቀ ጨዋማ ውሃ መጉመጥመጥ ባክቴሪያዎችን ይቀንሳል፤ እንዲሁም የድድ መድማትን ያቆማል።
8. ግሪን ቲ( አረንጓዴ ሻይ ይጠጡ)፦ አረንጓዴ ሻይ በየቀኑ መጠጣት በጥርስ ዙሪያ ህመምና የድድ መድማትን ሊያቆም ይችላል። አረንጓዴ ሻይ በተፈጥሮ ካቴቺን የሚባል አንቲኦክሲዳንት የያዘ ሲሆን በባክቴሪያ ምክንያት የሚከሰትን የድድ መቆጣት ይቀንሳል።
9. ጭንቀትን መቀነስ፦ ጭንቀት የሰዉነትን የህመም መከላከል አቅምን ይቀንሳል። ይህ የባክቴሪያ ኢንፌክሽንን መከላከል አስቸጋሪ ያደርገዋል