094 046 4646/0940 565656    
info@sainturaelclinic.com
Follow Us:

View Blog

የደም ቅዳ የደም ቧንቧዎች የህመም ምልክቶች

ክፍል ሁለት

የህመም ምልክቶቹ ቀስ በቀስ በሂዳት የሚከሰት ሲሆን በቶሎ ላይታይ ይችላል።በብዙ ሰዎች ላይ የደም ቅዳው ከ60 ፐርሰንትና ከዚያን በላይ ካልጠበበ በስተቀር የህመም ምልክቶች ላይታዩ ይችላሉ። የመጀመሪያዉ ሊታይ ከሚችሉ ህመም ምልክቶች ዉሰጥ አንዱ እየመጣ የሚሄድ ጡንቻዎች ህመም መከሰት( ኢንተርሚታንት ክላዉዲኬሽን) ሲሆን ይህም እንቅስቃሴ ሲያደርጉ በእግር ጢንቻዎች ላይ ምቾት ማጣት፣ህመም ወይም ቁርጥማት ስሜት መከሰትና እረፍት ሲያደርጉ የህመም ስሜቱ መጥፋት ናቸው። የህመም ስሜቱ በብዛት የሚከሰተዉ በታፋ ጡንቻዎች ላይ ቢሆንም አልፎ አልፎ በዳሌና በጭን ጡንቻዎች ላይ ይከሰታል። ከላይ ከዘረዘርናቸዉ የህመም ምልክቶች በተጨማሪ የመደንዘዝ፣የመክበድ፣ የጡንቻዎቹ መዛል ወይም መድከም ስሜቶች ሊከሰት ይችላል። የህመም ስሜቶቹ በእንቅስቃሴ ሰዓት የሚባባሱ ሲሆን እረፍት ሲያደርጉ ይጠፋል ወይም ይታገሳል። ህመሙ እየከፋ ሲሄድ ኖርማል የእግር ጉዞ ሲያደርጉ ከመባባሱ የተነሳ አንቅስቃሴ ከማድረግ ሊያግዶት ይችላል። የህመም ምልክቶቹ እንዲከሰት የሚያደርገዉ በደም ቧንቧዎቹ ጥበት የተነሳ ወደ እግር ጡንቻዎች የሚሄደዉ የደም ዝዉዉር ስለሚቀንስ ሲሆን እረፍት ሲያደርጉ የህመም ስሜቶቹ የሚቀንሱት በእረፍት ወቅት የእግር ጡንቻዎች የሚፈልጉት የደም ዝዉዉር ስለሚቀንስ ነዉ። ሌሎች የህምመ ምልክቶቸ ደግሞ

·         በተለይ ማታ ማታ ጋደም በሚሉበት ወቅት በእግርዎ መዳፍና ጣቶች ላይ የማቃጠል ወይም ህመም ስሜት መከሰት

·         የእግር መዳፍና ታችኛዉ እግር ክፍል ላይ መቀዝቀዝ

·         የቆዳ ቀለም መቀየር( መቅላት ወይም ሌላ ቀለም መከሰት)

·         የእግርና የእግር ጣቶች ላይ ቁስል ሲከሰት መቶሎ ያለመዳን

·         የኢንፌክሽን በተደጋጋሚ መከሰት ናቸዉ።

ብዙዎቹ የዉጨኛዉ ደም ቅዳ የደም ቧንቧ ችግር ያለባቸዉ ሰዎች ምንም የህመም ስሜት ላይኖራቸዉ ይችላል።

ህክምና                                  

ለዉጨኛዉ የደም ቅዳ ደም ቧንቧዎች ችግር ሊደረጉ ከሚችሉ ህክምናዎች ዉስጥ የኗኗር ዘይቤ ለዉጥ ፣ መድሃኒቶችና የቀዶ ጥገና( ኢንተርቬንሽናል ፕሮሲጀሮች) ተተቃሾች ናቸዉ።

·         መድሃኒቶች ፦ የደም ግፊት፣የስኳር፣ ኮሌስትሮልና የደም መርጋትን የሚከላከሉ እንደ አስፒሪን ያሉ መድሃኒቶችን በህክምና ባለሙያዎ ትእዛዝ መሰረት መዉሰድ

·         ፕሮሲጀሮች፦ ባሎን አንጂዎግራፊ፣ ስቴንና በይፓስ ሰርጀሪና የመሳሰሉት ናቸዉ።

 

መከላከል

·         የተመጣጠኑ ምግቦችን መመገብ;- ከፍተኛ የፋይበር መጠንና ዝቅተኛ የኮሌስትሮል፣ ስብና ጨዉ መጠን ያላቸዉ ምግቦችን መመገብ

·         ሲጋራ አለማጨስ ወይም እያጨሱ ከሆነ  ማቆም

·         የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ

·         የታወቁ ህመሞችን በአግባቡ መታከም፦ የደም ግፊትና ስኳር ህመሞች ካሉ በአግባቡ መታከም ያስፈልጋል

·         ኢንፌክሽኖችን ለመክላከልና ለመቀነስ እግርዎንና የእግር ቆዳዎን በደንብ መንከባከብ

Share with: