ማንኮራፋትን ለመቀነስ የሚራዱ ቀላል መንገዶች
· የሰዉነት ክብዳትዎ ከፍተኛ ከሆነ ክብደትዎን መቀነስ፦ ከመጠን በላይ ወፍራም የሆኑ ሰዎች ለማንኮራፋት አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ተጨማሪ ቲሹዎች(ስጋዎች) በጉሮሮ ውስጥ ሊኖራቸው ይችላል። የሰዉነት ክብደትን መቀነስ ማንኮራፋትን ለመቀነስ ይረዳል።
· ሲተኙ በጎን በኩል ይሁን፦ በጀርባዎ መተኛት ምላስዎ ወደ ጉሮሮዎ ወደ ኋላ እንዲሰበሰብ ስለሚያደርግ የአየር መተላለፊያ ቱቦዎን በማጥበብና የአየር መተላለፍን በከፊል እንዲዘጋ ያደርገዋል። በጎንዎ ለመተኛት ይሞክሩ።
· የአልጋዎን ራስጌ ከፍ ማድረግ፦ የአልጋዎን ራስጌ በ10.16cm ወይም 4 ኢንች አካባቢ ማሳደግ ሊረዳዎ ይችላል።