094 046 4646/0940 565656    
info@sainturaelclinic.com
Follow Us:

View Blog

የጉበት ስብ መሆን (Fatty Liver)

ክፍል አንድ

የጉበት ስብ መሆን በሽታ በብዛት የሚከሰት ሲሆን በጉበት ውስጥ ከመጠን በላይ ስብ በሚከማችበት ወቅት የሚከሰት የተለመደ በሽታ ነው።ጤናማ ጉበት ትንሽ መጠን ያለው ስብ ይይዛል ወይም ይኖረዋል። የጉበት የስብ መጠኑ ከ5% እስከ 10% የጉበቱ ክብደት ሲደርስ ወይም ሲሸፍን ችግር ያመጣል።

በአብዛኛዎቹ ጊዜያት የጉበት ስብ መሆን በሽታ ምንም አይነት ከባድ የህመም ችግር አይፈጥርም ወይም ጉበትዎ በተለምዶ ከሚሰራዉ ስራ እንዳያከናዉን አያግደውም። ነገር ግን ከ 7 እስከ 30 በመቶ በሚሆኑት ሰዎች ላይ የጉበት ስብ መሆን በሽታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰ ይሄዳል። ይህም ሦስት ደረጃዎች ያልፋል፡-

1.      ጉበትዎ ይቆጣል( ያብጣል)-ይህም ጉበቱ አንዲጎዳ ያደርጋል።ይህም ስታቲዎሄፓታይቲስ ይባለል

2.     ጉበትዎ የተጎዳበት አካባቢ ጉበትዎ ላይ ጠባሳ መፍጠር-- ይህ ፋይብሮሲስ ይባላል

3.     በጣም ብዙና ሰፊ ወይም አብዛኛዉ ጤናማ የጉበት ክፍል (ቲሹ) በጠባሳ መተካት--ይህ የጉበት መድከም ወይም ሲርሆሲስ ደረጃ ይባላል

ጉበት ሃሞትን ያመርታል፣ለሰዉነታችን ፕሮቲን ያዘጋጃል፣የብረት መዕድንን ያጠራቅማል ደም እንዲረጋ የሚያደርጉ ንጥረ ነገሮችን ያመርታል፣ ለበሽታ መከላከል የሚያገለግሉ ንጥረ-ነግሮችን ያመርታል እንዲሁም ከደም ዉስጥ ጎጂ ኬሚካሎችን ያስወግዳል።

ሁለት አይነት የጉበት ስብ መሆን ችግሮች አሉ                                      

1.      በአልኮል ምክንያት የሚከሰት የጉበት ስብ መሆን (Alcoholic liver disease)ና፡- ይህ የአልኮሆል መጠጦችን  በከፍተኛ መጠን አዘዉትረዉ በመጠጣት ምክንያት  በጉበታቸዉ ላይ ስብ በሚጠራቀምበት ወቅት ነዉ።

2.     ከአልኮሆል ዉጪ ባሉ ምክንያቶች የጉበት ስብ መሆን ችግሮች (Nonalcoholic fatty liver disease) ናቸዉ። ይህ ምን እንደሚያመጣዉ በዉል ባይታወቅም የሰዉነት ክብዳት መጨመር( ዉፍረትና) የስኳር ህመም ያላቸዉ ሰዎች ለችግሩ ይበልጥ ተጋላጭ ናቸዉ።

ለጉበት ስብ መሆን ችግር መንስዔዎች      

አንዳንድ ሰዎች ምንም ዓይነት  ቅድመ አጋላጭ ሁኔታዎች ሳይኖራቸው የጉበት ስብ መሆን ችግር ይገጥማቸዋል። ለጉበት ስብ መሆን ችግር መንስዔ ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮች

·         የሰዉነት ክብደት መጠን መጨመር ወይም ወፍራም መሆን

·         አይነት ሁለት የስኳር ህመም መኖር

·         ሜታቦሊክ ሲንድረም ያላቸዉ ሰዎች( ከፍተኛ የደም ግፊት፣የኮሌስትሮልና ትራይግላሴራይድ የደም ስብ መጠን ከፍተኛ መሆን፣ ሰዉነታችን ኢንሱሊንን አልቀበል ሲል( ኢንሱሊን ሬሲስታንስ)) ናቸዉ።

·         መድሃኒቶች፦ አሚዳሮን፣ ዲልታዜም፣ ታሞክሲፌንና ስቴሮይዶች የሚወስዱ ከሆነ



Share with: