094 046 4646/0940 565656    
info@sainturaelclinic.com
Follow Us:

View Blog

ቴምርና የጤና ጥቅሞቹ


ቴምር በብዙ የዓለም ሞቃታማ አካባቢዎች ከሚበቅል ከቴምር ዛፍ የሚገኝ ፍሬ ነው። ቴምር ጣፋጭና የሚታኘክ ፍሬ ሲሆን እንደ ኃይል ወይም ጉልበትና በሰውነት ውስጥ የብረት ማዕድን ለመጨመር እንዲሁም የምግብ መፈጨት ስርዓትን በመርዳትና የመሳሰሉት በጣም ጥሩ የሆነ የጤና ጥቅሞች አሉት።ቴምር በብዙ የምግብ ንጥረነገሮች ፈይበርና አንቲኦክሲዳንት የበለፀገ ነዉ። እንደ ቴምር አይነቱ ቢለያይም እያንዳንዱ ቴምር ከ60 አስከ 70 በመቶ የሚሆነዉ ስኳርና ከፍተኛ ፋይበር ስልሆነ ለሀይል ምንጭነት ተመራጭ ያደርገዋል።ቴምር ከፍተኛ የብረት ማዕድን ስላለዉ የደም ማነስን ለመከላከል ይረዳል።


ቴምር ለጅዉሶች፣ለኬክ፣ ማፍል፣ ስሙዚዎች ዉስጥ ለተፈጥሮ ማጣፈጫነት ያገለግላል።

ቴምር ጥሩ የሀይል፣ፈይበር፣ ስኳርና የተለያዩ ቫይታሚኒች ምንጭ ነዉ። ቴምር በጣም አስፈላጊ የሆኑ እንደ ካልሲየም፣ ብረት፣ ፎስፈረስ፣ ሶዲየም፣ ፖታሲየም፣ ማግኒዚያም፣ ድኝና ዚንክ ያሉ ማዕድኖችን ይይዛል። ከላይ ከተጠቀሱት ንጥረ ነገሮች በተጨማሪ እንደ ቲያሚን፣ ሪቦፍላቪን፣ ኒያሲን፣ ቫይታሚን B6፣ ፎሌት፣ ቫይታሚን ኤ እና ቫይታሚን ኬ ያሉ ጠቃሚ ቪታሚኖችን ሊይዙ ይችላሉ።

የጤና ጥቅሞቹ

1. ጥሩ የሀይል ሰጪ ምንጭ ነዉ፦ ቴምር ከፍተኛ የተፈጥሮ ስኳር የሆኑ ጉሉኮስ፣ ፍሩክቶስና ሱክሮስ ምንጭ ነዉ።

2. ለአዕምሮ ጤንነትን ለመጠበቅ፦ ቴምር የአዕምሮ መቆጣትንና ኦክሲዳቲቭ ስትረስን ለመከላከል ይረዳል። ቴምር የፋይበር ምንጭ ሲሆን በተፈጥሮ አንቲኦክሲዳንትና በፌኖሊክስ የበለፀገ ነዉ፡ የፖሊፌኖሊክ ድብልቆች መኖር አልዚሄመርና ዲሜንሽያ ህመምችን ለማዘግየትና ለመቀነስ ይረዳል።

3. የአንጀት ድርቀትን ለመቀነስና ለማስታገስ፦ ቴምር ከፍተኛ የሆነ ፋይበር አለዉ ( በተለይ በዉሃ የማይሟሙ ፋይበሮች)። ይህ የምግብ መፈጨትን በመርዳትና የአንጀት ድርቀትን ለመቀነስ ይረዳል።

4. የደም ማነስን ለመቀነስ፦ ቴምር ጥሩ የብረት ማዕድን ምንጭ ነዉ። ስለሆነም ቴምርን መመገብ የደም ማነስ ምልክቶችን ለመቀነስ ይረዳል።

5. የልብ ህመምን ለመቀነስ፦ ቴምር ትራይግለይሴራይድ የስብ አይነትንና ኦክሲዳቲቭ ስትረስን ለመቀነስ ይረዳል። ይህም የልብ ችግሮችን ለመቀነስ ይረዳል።

6. ለአጥንት ጤንነት፦ ቴምር ፎስፈረስ፣ ፖታሲያም፣ ካልሲየምና ማግኒዚየም የመሳሰሉት መዕድናትን ይይዛል። ይህ የአጥንት መሳሳትን ለመክላከል ይረዳል።

7. የደም ስኳር መጠንን ለመቆጣጠር፦ ቴምር ዝቅተኛ ግላይሴሚክ ኢንዴክስ፣ ከፍተኛ ፋይበርና አንቲኦክሲደንቶች ስላው በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ለመቆጣጠር የሚያስችል አቅም አለው።


Share with: