094 046 4646/0940 565656    
info@sainturaelclinic.com
Follow Us:

View Blog

ካንሰርን መከላከል

የካንሰር ስጋትዎን ለመቀነስ የሚጠቅሙ 7 ምክሮች

እንደሚታወቀዉ ጥር 27( ፌብሪዋሪ 4) አለም አቀፍ የካንሰር ቀን ነዉ። ይህም በአለም አቀፍ ደረጃ  የካንሰርን ግንዛቤ ለማሳደግ አንዲሁም መከላከልን፣ የካንሰር ምርመራንና ህክምናውን ለማበረታታት ያግዛል።

እንደ አለም አቀፍ የጤና ድርጅት መረጃ እ.ኤ.አ. በ 2020 ካንሰር በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሞት የሚዳርግ ዋነኛ መንስኤ ሲሆን 10 ሚሊዮን የሚጠጋ ሞት ፣ ወይም ከስድስት ሞት ውስጥ አንዱ  የሞት ምክንያት የሆነው ካንሰር ነበር።

የሳንባ፣ የፕሮስቴት እጢ፣ የትልቁ አንጀት፣ የጨጓራና የጉበት ካንሰር በወንዶች ላይ በብዛት የሚከሰቱ የካንሰር አይነቶች ሲሆኑ የጡት፣ የትልቁ አንጀት፣ የሳንባ፣ የማኅጸን ጫፍና የታይሮይድ ካንሰሮች በሴቶች ላይ በብዛት ይጠቀሳሉ።

ካንሰርን መከላከል

1.      ሲጋራ ከማጨስ መቆጠብ፦ ማንኛውንም የትምባሆ አይነት መጠቀም የካንሰር ተጋላጭነትዎን ይጨምራል። ሲጋራ ከአፍ፣ሳንባ፣ ጉሮሮ፣ቆሽት፣የሽንት ፊኛ፣ የማህፀን አንገትና ኩላሊት ካንሰር መከሰት ጋር ግንኙነት አለዉ። ምንም እንኳ ሲጋራ የማያጨሱ ቢሆኑም ለሲጋራ ጭስ የተጋለጡ ከሆነ ለካንሰር የመጋለጥ ዕድልዎ ከፍተኛ ነዉ። ሲጋራ ከማጨስ ይቆጠቡ ወይም እይስጨሱ ከሆነ ያቁሙ። ለሲጋራ ጭስ ከመጋለጥም ይቆጠቡ።

2.     ጤናማ አመጋገብን ይከተሉ፦

·         አትክልትና ፍራፍሬን አብዝተዉ ይጠቀሙ

·         የሰዉነት ክብደትዎን ይቀንሱ ወይም ያመጣጥኑ

·         መጠጥ አይጠጡ አሊያም በመጠኑ ያድርጉ

·         የተቀነባብሩ የስጋ ዉጤቶችን ይመጥኑ

3.     ጤናማ የሰዉነት ክብደት ይኑርዎ አንዲሁም አካላዊ እንቅስቃሴ ያድርጉ፦ ጤናማ ክብደት እንዲኖርዎ ማድረግ ወይም የሰዉነትዎን ክብደት ጤንነት መጠበቅ የጡት፣ የፕሮስቴት ፣ የሳንባ፣ የአንጀት እና የኩላሊት ካንሰርን ጨምሮ ለተለያዩ የካንሰር አይነቶች ተጋላጭነትን ይቀንሳል። የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግም ካንሰርን ከመከላከል ረገድ ትልቅ ጥቅም አለዉ(በተለይ የጡትና የአንጀት ካንሰርን ለመከላከል)።

4.     እራስዎን ከፀሃይ ብርሃን መከላከል፡-  የቆዳ ካንሰር በጣም ከተለመዱት የካንሰር ዓይነቶች አንዱ ነው - እናም በጣም መከላከል ከሚቻሉት ውስጥ አንዱ ነው።

5.     ክትባት መዉሰድ፦ ክትባት በመዉሰድ ልንከላከላቸዉ ክምንችላቸዉ የካንሰር አይነቶች ዉስጥ የጉበትና የማህፀን ጫፍ ካንሰሮች ናቸዉ። ስለሆነም ልጉበት ቫይረስ ቢ(HBV)ና የማህፀን ጫፍ ካንሰር ምከለከያ ክትባት( Human papillomavirus (HPV) ክትባት ይዉሰዱ።

6.     አደገኛ ባህሪያትን ያስወግዱ፦ ለምሳሌ ልቅ የሆን የግብረ-ስጋ ግንኙነት ከማድረግ ይቆጠቡ፤ መርፌን ጨምሮ ስለታማ ነገሮችንና የጥርስ ብሩሾችን በጋራ ከመጠቀም መቆጠብ

7.     መደበኛ የጤና ክትትል ማድረግ፦ መደበኛ የጤና ክትትልና የካንሰር ምርመራዎችን ማድረግ በተለይ የጡት፣ የአንጀት፣ የማህፀን ጫፍና የቆዳ ካንሰር ምርመራዎችን በመደበኛነት ሀኪምዎ ጋ ቀርበሁ ምርመራና ክትትል  ማድራግ ይገባል።



Share with: