ማንኮራፋት በጉሮሮዎ ውስጥ ከሚገኙት በላሉ ክፍሎች ውስጥ አየር ሲያልፍ የሚፈጠረው ኃይለኛ ድምጽ ሲሆን ይህም በሚተነፍሱበት ጊዜ የላሉት የጉሮሮ ቲሹዎች(ክፍሎች) እንዲርገበገቡ ያደርጋል። ማንኮራፋት ማንኛዉም ሰዉ ሊገጥመዉ የሚችለዉ ችግር ቢሆንም አንድ አንድ ሰዎች ላይ ግን ስር የሰደደና አንዳንዴም ከባድ የጤና ሁኔታን ሊያመለክት ይችላል።
የህመም ምልክቶች
ማንኮራፋት ከእንቅልፍ ችግሮች ጋር ሊገናኝ የሚችል ሲሆን ይህም ኦብስትራክቲቭ ስሊፕ አፕኒያ ይባላል። ምንም እንኳ የሚያንኮራፉ ሰዎች ሁሉ ኦብስትራክቲቭ ስሊፕ አፕኒያ ይኖራቸዋል ባይባልም ከማንኮራፋት ጋር ተያይዞ የሚከተሉት የህመም ምልክቶች ካለዎ ይህክምና ባለሙያዎን ያማክሩ፦
· በሚታኑበት ወቅት የአተነፋፈስ መቆራረጥ ካስተዋሉ
· ቀን ቀን የበዛ እንቅልፍ እንቅልፍ ማለት
· ትኩራት ማድራግ መቸገር
· የጠዋት ራስ ምታት
· በአንቅል ሰዓት ትንታ መኖር ወይም አየር ማጠር
· ከፍተኛ የደም ግፊት
· ማታ ማታ የደረት ህመም መኖር
· ሲያንኮራፎ ድምፁ ከፍተኛ በመሆኑ አብሮ የሚተኙትን የሚረብሽ ከሆነ
· በልጆች ላይ ትክረት ካሩ፣የባህሪ ለዉጥ አሊያም የትምህርት ዉጤት መቀነስ ካላቸዉ ናቸዉ።
ኦብስትራክቲቭ ስሊፕ አፕኒያ መገለጫ የሆነዉ ተኝተዉ ሲያንኮራፉ ድምፁ ከፍተኛ ሲሆን በመሃሉ ፀጥ ይሉና መተንፈስ ያቆማሉ ወይም በጣም ዝግተኛ ይሆናል። በመጨረሻም ይህ የትንፋሽ መቀነስ ወይም ለአፍታ ማቆም ከእንቅልፍዎ ለመነሳት ምልክት ሊሰጥዎት ይችላል፣ እናም እርስዎም በከባድ ድምፅ በማንኮራፋት ወይም በሚተነፍስ ከእንቅልፍዎ ሊነቁ ይችላሉ።
መንሴኤዎች
· የአፍንጫ ችግሮች ካሉ፦ የአፍንጫ መዘጋት ወይም መጠቅጠቅ
· የእንቅልፍ ማጣት፦ በቂ እንቅልፍ ያለማግኘት የጉሮሮ አካላት ይበልጥ እንዲላሉ ስለሚያደርግ ማንኮራፋትን ሊያባብስ ይችላል።
· የአተኛኘት ሁኔታ፦ በጀርባዎ መተኛት የአየር መንገዱን ስለሚጠብበው ማንኮራፋቱ በጣም ተደጋጋሚና በፍተኛ ድምጽ ሊሆን ይችላል።
· የአልኮኮል መጠጥ፦ ከመተኛትዎ በፊት ከመጠን በላይ አልኮል መውሰድ ለማንኮራፋት ችግር መንሴ ነዉ።
የአፍ ዉስጥ አካላት ተፈጥሮ፦ ዝቅ ያለ ወፍራም ለስላሳ ላንቃ መኖር የአየር መንገዱን ጠባብ ያደርገዋል።ረጅም እንጥል ካለዎ ከመጠን በላይ ወፍራም የሆኑ ሰዎች በጉሮሮአቸው ጀርባ ላይ ተጨማሪ ስጋ ሊኖራቸው ይችላል፤ ይህም የአየር መንገዶቻቸውን ሊያጠብ ይችላል። በተጨማሪም የእንጥል መርዘም ካለዎ የአየር ፍሰት ሊያግድና ንዝረት ሊጨምር ይችላል።