የህመም ምልክቶች
ክፍል ሁለት
የጉበት ስብ መሆን ችግር ያለባቸዉ ሰዎች ህመሙ ስር ሰዶ ስሪሆሲስ የሚባለዉ የጉበት መድከም ደረጃ ላይ እስኪደርስ ድረስ ምንም አይነት የህምመ ምልክቶች ላይኖራቸዉ ይችላል። የህመም ምልክቶች ከተከሰቱም የሚከተሉትን ሊያጠቃልል ይችላል፦
· የሆድ ህመም ወይም በቀኝ የላይኛዉ የሆድዎ ክፍል የሆድ መጠን መጨመር ስሜት መኖር
· ማቅለሽለሽ፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ ወይም የሰዉነት ክብደት መቀነስ መከሰት
· የቆዳና አይን ነጩ ክፍል ቢጫ መሆን
· የሆድና የእግር ማበጥ ምልክቶች
· ከፍተኛ ድካም ናቸዉ።
ሊደረግ የሚችል ህክምና
ለጉበት ስብ መሆን ችግር በቀጥታ ሊሆን የሚችል ህክምና የለም። ይሁንና ልችግሩ መከሰት መንስኤ የሆኑ ምክንያቶችን በመቆጣጠር ችግሩን መቀነስ ይቻላል። በተጨማሪም የአኗኗር ዘይቤ ለዉጦችን ማድረግ የጤንነትዎን ሁኔታ ሊያሻሽሉ ይችላሉ። ሊደረጉ ከሚችሉ ነገሮች ዉስጥ
· የአልኮሆል መጠጥን ሙሉ በሙሉ ማስወገድ
· የሰዉነት ክብደትዎን መቀነስ
· ስኳር፣ የስብ መጠን ከፍ ማለት(ኮሌስትሮልና ትራይግላይሴራይድ)ና ሌሎች የህመም ችግሮች ካለዎ መድሃኒት በአግባቡ መወሰድ
· ለተወሰኑ ችግሮች ቫይታሚን ኢ መዉሰድ ናቸዉ።
የጉበት ስብ መሆን ችግር ያላቸዉ ሰዎች እንዲመገቡ የሚመከሩ ምግቦች
· የተመጣጡኑ ምግቦችን መመገብ፦ ከሁሉም የምግብ ምድቦች ውስጥ ምግቦችን በመምረጥ ለመመገብ ይሞክሩ. ይህም አትክልትና ፍራፍሬ፣ የእህል ዘሮች፣ ፕሮቲኖች፣ አነስተኛ ቅባት ያላቸው የወተት ተዋጽኦዎች፣ እና ጤናማ ቅባቶች እና ዘይቶችን ይጨምራል።
· የካሎሪ መጠናቸዉ ከፍተኛ የሆኑ ምግቦችን መቀነስ፦ ከፍተኛ የካሎሪ ይዘት ያላቸውን ምግቦች አጠቃቀምዎን ለመገደብ ያስቡ።
· የፋይበር ይዘታቸዉ ከፍተኛ የሆኑ ምግቦችን በብዛት መመገብ፦ ፋይበር የጉበት የመስራት አቅምን ይጨምራል።
§ ጨዉ የባዛበት ምግቦች፦
§ በፋብሪካ የተቀነባበሩ ወይም የተጣራ ሀይል ሰጪ/ ካርቦሀይድሬቶችዝ(ጣፋጭ፣ ነጭ ሩዝ፣ ነጭ ዳቦና ሌሎች የተጣሩ ካርቦሀይድሬቶች)
§ ጤናማ ያልሆኑ ስቦች (ሳቱሬትድና ትራንስ የስብ አይነቶች) ካላቸዉ
መከላከል
የጉበት ስብ መሆን በሽታንና ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን ለመከላከል ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን መከተል አስፈላጊ ነው። አንዳንድ አጠቃላይ የመከላከያ ምክሮች የሚከተሉትን ያካትታሉ።
· አልኮሆል ከመጠጣት መቆጠብ ወይም ማቆም
· የሰዉነት ክብደትዎን መቆጣጠር
· የተመጣጠኑ ምግቦችን መመገብ፦ ሳቹሬትድ ፋት፣ትራንስ ፋትና የተጣሩ ካርቦሀይድሬቶችን የያዙ ምግቦችን መቀነስ
· የሰዉነት ስብና ስኳር መጠን ላይ ቁጥጥር ማድረግ
· የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ናቸዉ።