የጥርስ መቦርቦርና መበስበስ
የጥርስ መቦርቦር በጥርስ መበስበስ ምክንያት የሚከሰት ሲሆን ችግሩ በጊዜ ሂደት የሚመጣ ነዉ። የጥርስ መበስበስ እንዲከሰት የሚያደርጉ ነገሮች
·
በጥርሱ ላይ የሚጋገር ነገር ሲኖር፦ በጥርስ ላይ የሚጋገሩ ነገሮች የሚከሰቱት ብዙ ስኳርና ስታርቾችን ከተመገቡ
በኃላ ጥርስዎን በደንብ ባለማጽዳት ምክንያት ነው።ስኳርና ስታርቾች
ከጥርሶችዎ ላይ ካልፀዱ ባክቴሪያዎቹ በፍጥነት ይመገቡትና ጥርሱ ላይ ንጣፍ ይፈጥራሉ። በጥርሶችዎ ላይ የሚቆዩ ንጣፎች ከድድ መስመርዎ ስር
ወይም በላይ በመጠራቀም ጠንካራ ነገር ይፈጥራሉ። ይህም ጠንካራ ንጣፉን ለማስወገድ የበለጠ አስቸጋሪ ከማድረጉም በላይ ለባክቴሪያዎች መከላከያ ሆኖ ያገለግላል።
·
የንጣፉ ጥርስን መጉዳት፦ በንጣፉ ዉስጥ ያለዉ አሲድ በጥርስዎ ጠንካራ ክፍል ወይም ኢናሜል ላይ ጉዳት በማድረስ መዓድኖችን ያስወግዳል። ይህ ትናንሸ ቀዳዳዎችን በጥርሱ
ላይ እንዲፈጠሩ ያደርጋል። ኢናሜሉ ከተጎዳ በኃላ ባክቲሪያዎቹና አሲዱ ቀጣዩን የጥርስ ንጣፍ( ዴንቲን)ና ለስላሳዉን የጥርስ
ክፍል ያገኙታል። ይህ ክፍል ከጥርስ ስርና ነርቭ ሩት ጋር ቀጥታ ግንኙነት የሚያደርገዉ ክፍል ነው።
- የጉዳቱ መቀጠል፦ አንዴ ጥርሱ መበስበስ ከጀመረ ባክቴሪያና አሲዱ የሚያደርጉትን
ጉዳት በመቀጠል የዉስጠኛዉ የጥርስ ክፍል የሆነዉንና የደም ቧንቧና ነርቮችን ያያዘዉ ክፍል ወይም
ፐልፕ ላይ ጉዳት ማድረስ ይጀምራሉ። በዚህም ምክንያት ፐልፑ ያብጣል፣ይቆጣል፣ ነርቩ ህመም እንዲመጣ ያደርጋል። ህመሙ
ከጥርሱ አልፎ አጥንቱ ላይ መሰማት ይጀምራል።
አጋላጭ ምክንያቶች
ማንኛዉም ጥርስ ያለዉ
ሰዉ የጥርስ መቦርቦር መከሰት ተጋላጭ ቢሆንም የሚከተሉት ምክንያቶች ለችግሩ ይበልጥ ተጋላጭ ያደርጉዎታል፦
·
የጥርሱ ቦታ፦ የጥርስ መበስበስ በብዛት የሚከሰተዉ ከፊትለፊት ጥርሶች ይልቅ በሰተጀርባ ባሉ መንጋጋ
ጥርሶች ላይ ነዉ። የመንጋጋ ጥርሶች የምግብ ቅንጣቶች ሊጠራቀሙበት የሚችሉ ብዙ ጎድጓዳ ቦታዎች ሰላላቸዉና በደንብ ለማፅዳት አስቸጋሪ ናቸው።
·
የተወሰኑ ምግቦችና መጠጦች፦ በጥርስዎ
ላይ ረዘም ላለ ጊዜ ሊለጠፉ የሚችሉ ምግቦች እንደ ወተት፣ አይስክሬም፣ ማር፣ስኳር፣ሶዳ፣ የደረቁ ፍራፍሬዎች፣ ኬክ፣ ከረሜላዎችና
ችፕሶች በቀላሉ በምራቅ ከሚለቁት ወይም ከሚታጠቡት ይልቅ የጥርስ መበስበስ እንዲከሰት ያደርጋሉ።
- በተደጋጋሚ የሚጎነጩ ነገሮችንና መክሰስ መጠቀም፦ ስኳር የበዛባቸው
መጠጦችን ያለማቋረጥ ሲመገቡ ወይም ሲጠጡ፣ ጥርስዎን የሚያጠቁ እና የሚያደክሙ አሲዶችን ለማምረት ለአፍ ባክቴሪያ
ተጨማሪ ጉልበት ይሰጣሉ።
- ልጆችን በእንቅልፍ ላይ እያሉ መመገብ፦ ህፃናትን እንቅልፍ ተኝተዉ
ሳለ ወተትን ጨምሮ ስኳር ያላባቸዉ ፈሳሾችን በጡጦ
መመገብ ምግቡ ጥርሳቸዉ ላይ ብዙ ሰዓታት አንዲቆይ ስለሚያደርግ ለጥርሳቸዉ መበስበስ ምክንያት ይሆናል።
- በበቂ መጠን ጥርስን ያለመቦረሽ፦ ጥርስዎን ከምግብና ከመጠጥ በኃላ የማያፀዱ ከሆነ ጥርስዎ ላይ ስለሚጋገር ጥርሱን ለጉዳት
ይዳርጋል
- በቂ ፍሎራይድ አለማግኘት፦ፍሎራይድ የጥርስን መቦርቦር አደጋ ሊቀንስ የሚችል ሲሆን ገና መቦርቦር
የጀመረ ጥርስም ካለ ለማስተካከል ይጠቅማል። ከዚህ የተነሳ የቧንቧ ዉሃ ፍሎራይድ የሚጨመርባት ሲሆን በጥርስ ሳሙናዎችና
የአፍ መጎመጥመጫ ፈሳሾች ዉስጥም ይገኛል። ነገር ግን በብዙዎቹ
ታሽገዉ በሚሸጡ ዉሃዎች ዉስጥ ፍሎራይ አይኖርም።
- ልጆችና በዕድሜ የገፉ ሰዎች ላይ፦ በጊዜ ብዛት ጥርስ እየወለቀና ድድም እየሸሸ ይሄዳል፤ ይህም ለጥርስ
ስሮች መበስበስ ይበልጥ ተጋላጭ ይሆናሉ። በተጨማሪም በእድሜ የገፉ ሰዎች የምራቅ መመንጨትን የሚቀንሱ መድሃኒቶችን ሊወስዱ
ይችላሉ። ይህም ለጥርስ መበስመስ ምክንያት ሊሆን ይችላል።
- የአፍ ድርቀት፦ የምራቅ መቀነስ ለአፍ ድርቀት ይዳርጋል። በምራቅ
ዉስጥ ያለዉ ኬሚካልም በበክቴሪያዎች የሚመረትን አሲድ ሊቀንሱ ይችላሉ።
- ቃር፦ ቃር ወይም ጋስትሮኢንተስቲናል ሪፍሌክስ ዲዚዝ የጨጓራ አሲድ
ወደላይ ተመልሶ በመምጣት የጥርስ ኢናሜልን ሊጎዳ ይችላል።
- የአመጋገብ ችግር ያለባቸዉ፦ አኖሬክሲያና ቡሌሚያ የሚባሉ የአመጋገብ
ችግር ያለባቸዉ ሰዎች ለጥርስ መቦርቦር ችግር ተጋላጭ ናቸዉ። በተደጋጋሚ ማስታወክ ካለ የጨጓራ አሲድ የጥርሱን ኢናሜል
በቀላሉ እንዲበላ ያደርገዋል። የአመጋገብ ችግር ያለባቸዉ ሰዎች ምራቅ የማምረት ችግርም ይኖራቸዋል።