ክፍል ሁለት
ጥሩ የአፍና የጥርስ ንፅህና አጠባበቅ የጥርስ መበስበስንና መብርቦርን ለመከላከል ይረዳዎታል። የጥርስ በቦርቦርን ለመከላከል የሚረዱ ምክሮች፦
· ከተመገቡና ከጠጡ በኃላ ፍሎራይድ ባለዉ የጥርስ ሳሙና መቦረሽ፦ ቢያንስ በቀን ሁለት ጊዜ፤ ከተቻለ ደግሞ ከእያንዳንዱ ምግብ በኋላ ጥርሶችዎን ይቦርሹ፣ ፍሎራይድ የያዘ የጥርስ ሳሙና ይጠቀሙ። በጥርሶችዎ መካከል ለማጽዳት ፍሎሲስ ይጠቀሙ( የጥርስ ማፅጃ መጠቀም)
· አፍዎን መጉመጥመጥ፦ ለጥርስ መበስበስና በቦርቦር ተጋላጭ ከሆኑ የጥርስ ሀኪምዎ በፍሎራይድ አንዲግሞጠሞጡ ሊያዝዎ ይችላል።
· በተደጋጋሚ መክሰስ ከመመገብና ከመጠጣት/በተደጋጋሚ ፉት የሚደረጉ ነገሮችን ማስወገድ
· የቧንቧ ዉሃ መጠጣት፦ለህብረተሰቡ የዉሃ አገልግሎት የሚሰጡ ብዙዎቹ የቧንቧ ዉሃዎች ፍሎራይድ ስለሚጨመርባቸዉ የጥርስ መቦርሞርና መበስበስን ይከላከላል። የታሸጉ ዉሃዎችን ብቻ የሚጠጡ ከሆነ ፍሎራይድ ስለማያገኙ የፍሎራይድ ጥቅምን ላያገኙ ይችላሉ።
· የጥርስ ሀኪምዎ ጋ መደበኛ ክትትል ማድረግ፡- ችግሮችን ለመከላከል ወይም ቀደም ብሎ ለመለየት የሚረዳ መደበኛ የአፍ ምርመራ ያድርጉ እንዲሁም በባለሙያ ጥርስዎን ያፀዱ።
· ለጥርስ ጤንነት ጠቃሚ የሆኑ ምግቦችን ይመገቡ፡-የተወሰኑ ምግቦችና ፈሳሾች ለጥርስ ጤንነት መልካም ናቸዉ።
· የፍሎራይድ ሕክምናዎችን ለማድረግ ያስቡ ወይም መዉሰድን ከግምት ውስጥ ያስገቡ፡- የጥርስ ሀኪምዎ ፍሎራይድን በመጠጥ ውሃና ከሌሎች ምንጮች በበቂ መጠን ካላገኙ የፍሎራይድ ህክምናዎችን እንዲያደርጉ ሊመክርዎ ይችላል።
· የፀረ-ባክቴሪያ ህክምና፡-በተለይ ለጥርስ መበስበስ ተጋላጭ ከሆኑ ጎጂ ከሆኑ የአፍዉስጥ ባክቴሪያዎች ለመከላከል የጥርስ ባለሙያዎ ስፔሻል ፀረባክቴሪያ መግሞጥመጫ ሊኣዙልዎ ይችላሉ።
ሊያመጣዉ የሚችለዉ የጎንዮሸ ጉዳት
የጥርስ መበስበስና መቦርቦር የተለምዱ ነገሮች ከመሆናቸዉ የተነሳ በቁምነገር ላያዩዋቸው ይችላሉ። ህጻናት ጥርሳቸው ላይ መቦርቦር ቢያገኙ ምንም ችግር እንደሌለውም ያስቡ ይሆናል። ይሁን እንጂ የጥርስ መቦርቦርና የጥርስ መበስበስ ከባድና ዘላቂ ችግሮች ሊያስከትሉ ይችላሉ(ቋሚ ጥርሳቸው ገና ለሌላቸው ልጆች እንኳን ቢሆን)። የጥርስ መቦርቦር ሊያመጣቸ ከሚችላቸዉ ችግሮች ዉስጥ
· ህመም
· በጥርስ ዙሪያ ዕብጠትና መግል መያዝ
· የጥርስ መጎዳት ወይም መሸራረፍ
· ለማኘክ መቸገር
· የጥርስ መግል መያዝ ሲሆኑ
የጥርስ መበስበስና መቦርቦር ከፍ እያለና እየተባባሰ ሲመጣ
· የጥርስ ህመሙ የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴዎ ሊያዉክ መቻል
· ምግብ ማኘክ በመቸገር ኣሊያም በህመሙ ምክንያት ክብደት መቀነስ ወይም የምግብ ዕጥረት መከሰት
· በጥርስ መግል መኖር የተነሳ የባክቴሪያ ኢንፌክሸን መከሰትና ክፍ ያለ ችግር መከሰት ናቸዉ።