094 046 4646/0940 565656    
info@sainturaelclinic.com
Follow Us:

View Blog

የአየር ወይም ጋዝ/ፈስ ለመቀነስ የሚረዱ ምክሮች

ጋዝ ወይም ፈስ ያስቸግሮታል? ያስጨንቅዎታልስ? እንግዲያዉስ የሚከተሉትን  ምክሮች ይተግብሩዋቸዉ

ጋዝ/አየር የተለመደ የህይወት ክፍልና ጤናማ የምግብ መፍጫ ሥርዓት ተፈጥሯዊ ውጤት ነው። በሰውነትዎ ውስጥ ያለው ወይም የተመረተዉ ጋዝ መውጣት አለበት። ብዙ ሰዎች በቀን ከ14 እስከ 23 ጊዜ ጋዝ ሊያወጡ ይችላሉ። ይህ ቁጥር ብዙ ሊመስል ይችላል፤ ነገር ግን ብዙዎቹ ሽታ የላቸዉም።

ከታች የሚወጣዉ ጋዝ በአብዛኛዉ ከምንበላዉና ከምንጠጣዉ ፈሳሽ ጋር የዋጥነዉ ጋዝ ነዉ። ቀኑን በሙሉ ሲጠጡና ሲበሉ አየር ይዉጣሉ። ሌላዉ ጋዝ ደግም የሚመጣዉ የምንመገበዉ ምግብ በአንጃታችን ዉስጥ ሲፈጭ ነዉ።

ጋዝ ማስወጣት ተፈጥሮያዊ ቢሆንም አንዳንዴ ምቾት ላይሰጥ ይችላል። ስለሆነም ጋዝን/ ፈስን ለመቀነስ የሚመከሩ ነገሮች

1.      ምግብ ሲመገቡ በቀስታና በአስተዉሎት ይሁን፡- በፍጥነት ሲበሉ ቀስ ብለው ከሚበሉበት ጊዜ የበለጠ አየር ይውጣሉ። እየተራመዱ ወይም እየሄዱ፣ መኪና ወይም ቢስክሌት እየነዱና በሌሎች ተግባራት ላይ ሳሉ ከመብላት ይቆጠቡ።

2.     ማስቲካ ከማኘክ ይቆጠቡ፦ ቀኑን ሙሉ ማስቲካ የሚያኝኩ ሰዎች ከማያኝኩት የበለጠ አየር ይውጣሉ። የአፍ ጠረንዎን መልካም አድርጎ ስለማቆየት የሚጨነቁ ከሆነ በምትኩ ከስኳር ነፃ የሆነ ሜንት ለመጠቀም  ይሞክሩ።

3.     ጋዝ በብዛት እንዲመረት የሚያደርጉ ምግቦችን ይቀንሱ ፦ የተወሰኑ ምግቦች ከሌሎች አንፃር ብዙ ጋዝ እንዲመረት ያደርጋሉ። የተወሰኑ ካርቦሃይድሬት( ሀይል ሰጪ) ምግቦች ብዙ ጋዝ እንዲመረት ያደርጋሉ። ጋዝ እንዲመረት ከሚያደርጉ ካርቦሃይድሬቶች ዉስጥ ፍሩክቶስ፣ ላክቶስ፣የማይሟሙ ፋይበሮች፣ስታርቾችና ዉስብስብ ስኳር ያላቸዉ ምግቦች ናቸዉ።

4.    የምግብ ያለመስማማት ( ፉድ ኢንቶለራንስ) መኖር፦ የአንጃታችን ምግብን አለመቻል ከምግብ ጋር በተያያዘ ከሚከሰት የምግብ አለርጂ ይለያል። ይህ የምግብ ያለመስማማት ተቅማጥ ፣ ጋዝ መብዛት፣ ሆድ መንፋትና ማቅለሽለሽ እንዲከሰት ያደርጋል። የተለመደው የምግብ ያለመስማማት ላክቶስ ኢንቶለራንስ ነዉ። ላክቶስ በወተትና ወተት ተዋፅኦዎ ዉስጥ ይገኛል።

5.     ሶዳ፣ ቢራና ሌሎች ካርቦኔትድ መጠጦችን ያስወግዱ፦ በካርቦኔትድ መጠጦች ወይም ፈሳሾች ዉስጥ ያለዉ ጋዝ ሰዎች ሲያገሱ የሚወጣ ቢሆንም የተቀረዉ ወደ አንጀታችን በመሄድ የጋዝ መጠን እንዲጨምር ያደርጋል። ሰለሆነም ካርቦኔትድ ፈሳሾችን ከመጠቀም ይልቅ ዉሃና ሌሎች ከስኳር ነፃ ፈሳሾችን ይጠቀሙ።

6.    ሲጋራ የሚያጨሱ ከሆነ ያቁሙ፦ ሲጋራም ይሁን ሌሎች የሚጨሱ ነገሮች ብዙ አየር እንዲዉጡ ያደርጋል።

7.     የአንጀት ድርቀት ካለዎ መፍትሄ ለመስጠት ይሞክሩ፦ ሰገራ የማይወጡ ከሆነ በትልቁ አንጀት ዉስጥ ያለዉ ባክቴሪያ ሰገራዉ ይበልጥ እንዲብላላ ያደርጋሉ፤ ይህም ብዙ ጋዝ እንዲመረትና ሽታ እንዲኖረዉ ያደርጋል። ስለሆነም ድርቀት እንዳይከሰት መከላከል ፤ ከተከሰተም መታከም ይገባል።

8.    የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፦ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን በሳምንት ከ4 እስከ 5 ጊዜ ማድራግ

9.    የተወሰኑ ኢንዛየሞችንና ፕሮባዮቲክሶችን መጠቀም


Share with: