094 046 4646/0940 565656    
info@sainturaelclinic.com
Follow Us:

View Blog

የወንድ ብልት መቆም ችግር

ክፍል አንድ

የብልት መቆም ችግር (የአቅም ማነስ) በግብረ ሥጋ ግንኙነት ወቅት የብልት በበቂ መጠን አለመጠንከርና በግንኙነት ወቅት ማቆየት አለመቻል ነው። የብልት መቆም ችግር አንዳንድ ጊዜ መከሰት እንደችግር ላይታይ ይችላል። የብልት መቆም ችግር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የሚመታ ከሆነ ሊያስጨንቅና በራስ መተማመንን ሊቀንስ ይችላል ። የዚሀ ሁኔታ መከሰት መሰረታዊ የሆነ የጤና ችግር ምክልክትም ሊሆን ስለሚችል ህክምና መዉሰድ ሊያስፈልግ ይችላል።

የህመም ምልክቶች

የብልት መቆም ችግር የህምመ ምልክቶች የሚከተሉትን ሊያጠቃልል ይችላል፦

·         የብልት አልቆም ማለት

·         ብልትዎ ከቆመ በኃላ ጠንክሮ አለመቀጠል

·         ይግብረስጋ ግንኙነት ፍላጎት መቀነስ ናቸዉ።

·         በተጨማሪም በራስ መተማመን መቀነስ፣ ድብታንና ተጣማሪዎቹ ላይ ትፅዕኖ መፍጠር

አጋላጭ ነገሮች

በዕድሜ እየገፉ ሲሄዱ ብልትዎ ለመቆም ብዙ ጊዜ ሊወስድና ከቆመም በኃላ  ያን ያህል ጠንካራ ላይሆን ይችላል።

በዙ ነገሮች ል፡አብልት መቆም ችግር አጋላጭ ሊሆንኑ ይችላሉ።

·         ህመም፦ በተለይ የልብና የስኳር ህመም

·         ሲጋራ ማጨስ፦ ይህ የደም ቅዳና ደም መልስ የደም ዉዉርን ይቀንሳል

·         የሰዉነት ክብደት ከመጠን በላይ መሆን

·         የተወሰኑ ህክምናዎች፦ በተለይ የፕሮስቴት ዕጢ ቀዶ ጥገናና የካንሰር የጨረር ህክምና

·         አደጋዎች፦ በተለይ ለብልት መቆም የሚያገለግሉ የደም ስሮችና ነርቮች ላይ ጉዳት መድረስ

·         መድሃኒቶች፦ በተለይ ለድብታ የሚሰጡ፣ የአለርቺ መድሃኒቶች( አንታይሂስታሚኖች)፣የደም ግፊት ማከሚያ መድሃኒቶችና ሊርሎችም

·         የስነልቦና ችግር መኖር፦ ጭንቀት፣ ድብርትና አንዛይቲ

·         የአልኮሆል መጠጥ፦ በተለይ ለረጅም ጊዜ ጠጪ መሆን ናቸዉ።


Share with: