094 046 4646/0940 565656    
info@sainturaelclinic.com
Follow Us:

View Blog

የብልት መቆም ችግርን የሚያመጡ ምክንያቶች

ክፍል ሁለት

የወንድ የወሲብ ፍላጎት ለመቀስቀስ ዉስብስብ ሂደቶች ያሉት ሲሆን በዚህም ሂደት ዉስጥ አንጎል፣ ሆርሞኖች፣ ስሜት( emotions), ነርቮች፣ ጡንቻዎችና የደም ቧንቧዎችን ይሳተፋሉ። የብልት መቆም ችግር ከነዚህ ምክንያቶች በአንዱ ሊከሰት ይችላል። በተመሳሳይም ጭንቀትና የአዕምሮ ጤና ስጋቶች የብልት መቆም ችግርን ሊያስከትሉ ወይም ሊያባብሱ ይችላሉ።

አንዳንድ ጊዜ አካላዊና ስነ ልቦናዊ ጉዳዮች ከተከሰቱ የብልት መቆም ችግርን ያስከትሉ።

አካላዊ የብልት መቆም ችግር ምክንያቶች

·         የልብ ህመም

·         የደም ስሮች ጥበት

·         ከፍተኛ የደም ግፊት

·         ስኳር ህመም መኖር

·         የሰዉነት ዉፍረት

·         ሜታቦሊክ ሲንድረም መኖር

·         ሲጋራ ማጨስ

·         መጠጥን ጨምሮ ሌሎች አደንዛዥ ነገሮችን መጠቀም

·         የእንቅልፍ ችግር መኖር

·         የቴስቴስትሮን ሆርሞን መጠን አነስተኛ መሆን

·         ለፕሮስቴት ዕጢ ማደግና ካንሰር ህክምና

ስነልቦናዊ ምክንያቶች

በርካታ ነገሮች የወሲብ ስሜትን ሊያስተጓጉሉና የብልት መቆም ችግርን ሊያስከትሉ ወይም ሊያባብሱ ይችላሉ። ከነዚህም ዉስጥ

·         ድብርት፣ መጨናነቅና ሌሎች የአዕምሮ ችግሮች

·         ጭንቅት

·         በውጥረት፣ በመጥፎ ግንኙነት ወይም በሌሎች ስጋቶች የተነሳ የግንኙነት ችግሮች መኖር ናቸዉ።

ህክምና

የብልት መቆም ችግርዎ መንስኤ፣ ክብደትና ማንኛውም ዋና አምጪ የጤና ሁኔታዎች ላይ በመመስረት የተለያዩ የህክምና አማራጮች ሊኖሩዎት ይችላሉ። ሊደረጉ ከሚችሉ ህክምናዎች ዉስጥ

·         በሀኪም ትዕዛዝ የሚወሰዱ የተለያዩ መድሃኒቶች

·         ፓምፖች

·         የአካል ብቃት እንቅስቃሴ

·         የስነልቦና ህክምና

·         ለችግሩ መከሰት ምክንያት የሆኑ መሰረታዊ አካላዊ ችግሮች ካሉ ህክምና መዉሰድ ናቸዉ።

መከላከል

የብልት መቆም ችግርን ለመከላከል ምርጡ መንገድ ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን መምረጥ ወይም መከተልና የጤና ችግር ካለዎ  መቆጣጠር ነው። ለምሳሌ:

·         ከህክምና ባልሙያዎ ጋር በመመካከር የስኳር፣ የልብና ሌሎች ስር የሰደዱ ህመሞች ካሉ ተገቢዉን ህክምና ማድረግ

·         መደበኛ የጤና ክትትልና ምርመራ ማድረግ

·         ሲጋራ ከማጨስ መቆጠብ፤ እያጨሱ ከሆነ ማቆም፣አንዲሁም አደንዛዥ ዕፆችን ከመጠቀም መቆጠብ

·         የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በመደበኛነት ማድረግ

·         አልኮሆል አለመጠጠት፤ የሚጠጡም ከሆነ መመጠን

·         ጭንቀትንና ድብርትን ለማስወገድ ወይም ለመቀነስ መሞከር ናቸዉ።


Share with: