094 046 4646/0940 565656    
info@sainturaelclinic.com
Follow Us:

View Blog

ፒካ

የምግብነት ባህሪ የሌላቸዉ ነገሮች ያምሮታል? ተመግበዉ ያዉቃሉ?

ፒካ በባህል እንደ ምግብ የማይቆጠሩ ነገሮችን አብዝቶ መሻትና ማንም ሳያስገድዳቸዉ ፈልገዉት እንደ ምግብ መመገብ ወይም መጠቀም ነው። በሌላ አነጋገር ፒካ ያለው ሰው ሌሎች ምግብ ብለው የማይቆጥሯቸውን ነገሮች ይመኛል ወይም ይበላል።አንዳንድ ሴቶች በእርግዝናቸዉ ወቅት ይህን አይነት ባህሪ (ፒካ) ሊያዳብሩ ይችላሉ።

ሶስት የፒካ አይነቶች አሉ። እነርሱም

1.      ጂኦፋጂ ( ወይም ጂኦፋጂያ)፦ ይህም ከመሬት የሚገኙ እንደ አፈር፣ ሸክላ አፈርና ከሸክላ የሚሰሩ ነገሮችን የሚመገቡ

2.     አሚሎፋጂ (ወይም አሚሎፋጂያ)፦ ይህ ያልበሰሉ ወይም ጥሬ ስታርች የሚመገቡ ለምሳሌ የበቆሎ ስታርች፣ ላዉንደሪ ስታርች፣ ጥሬ ሩዝ (ryzophagia)ና ዱቄትን የሚመገቡ።

3.     ፓጎፋጂ( ፓጎፋጆያ)፦ ከፍተኛ መጠን ያለው የበረዶ የሚመገቡ ናቸዉ።

ፒካ ያላቸው ሰዎች ብዙ አይነት ምግብነት የሌላቸዉ  ነገሮችን ለመመገብ ይጓጓሉ (ይፈልጋሉ) ወይም    ይበላሉ። በዙ ጊዜ ሊመገቧቸዉ ከሚችሉዋቸዉ ነገሮች ዉስጥ

·         በረዶ

·         ሸክላ አፈር

·         ቆሻሻ

·         ቾክ( ጠመኔ)

·         ሳሙና

·         ሳንቲም

·         የተቃጠሉ ክብሪቶች እንዲሁም

·         ፀጉር ናቸዉ።

መንስኤዎች

በጣም የተለመዱት የፒካ መንስኤዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ:-

·         እርግዝና

·         እንደ ኦቲዝምና የአእምሮ እክል ያሉ የእድገት ችግሮች ያላቸዉ

·         እንደ ስክዚዮፍሬኒያ ያሉ የስነ-አዕምሮ ችግር ያለባቸዉ

·         አንዳንድ ምግብ ያልሆኑ ንጥረ ነገሮችን እንደ ቅዱስ ወይም የመፈወስ ባህሪያት የሚያዩ ባህላዊ ደንቦች ያላቸዉ ቦታዎች

የምግብ እጥረት በተለይ የብረት ማዕድን እጥረት ሲኖር ናቸዉ።

Share with: