ክፍል አንድ
ምች በሀርፕስ ሲምፕሌክስ አይነት አንድ ቫይረስ (herpes simplex virus type 1 (HSV-1) ኢንፌክሽን አማካይነት የሚመጣ ህመም ነዉ። በከንፈሮችዎ ላይና በዙሪያው ባሉ ቦታዎች ላይ ጥቃቅን፣ ፈሳሽ የቋጠሩ ወይም የተሞሉ ሽፍታዎችን ይከሰታሉ። እነዚህ አሽፍታዎች ብዙውን ጊዜ አንድ ቦታ ላይ እጅብ ብለዉ ይወጣሉ። ምች ብዙውን ጊዜ ከሁለት እስከ ሶስት ሳምንታት ውስጥ ጠባሳ ሳይተዉ ይድናል።
ምች ከሰዉ ወደ ሰዉ የሚተላለፈው እንደ መሳምና ሌሎች የቅርብ ለቅርብ ግንኙነት እንዲኖር በሚያደርጉ መንገዶች ነዉ። ምችን መሉ በሙሉ የሚያድን መድኃኒት የለም፣ ነገር ግን ሕክምና ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ይረዳል። ህክምና ማድራግ የወደፊት የወረርሽኙን ድግግሞሽ፣ ርዝማኔና ክብደት ሊቀንስ ይችላል።
የህመም ምልክቶች
· ማሳከክና የመንዘር ስሜት፡- ብዙ ሰዎች ትንሽ፣ ጠጠር ያለ፣ ህመም ያለዉና ዉሃ የቋጠረ ነገር ከመታየቱና ፈሳሹ ከመፍሰሱ በፊት ለአንድ ቀን ወይም ከዚያ በላይ በከንፈሮቻቸው አካባቢ ማሳከክ፣ ማቃጠል ወይም መወጠር ይሰማቸዋል።
· ዉሃ መቋጠር፦ በፈሳሽ የተሞሉ ትናንሽ እብጠቶችብዙውን ጊዜ በከንፈሮችዎ ዳር ላይ ይፈነዳሉ። አንዳንድ ጊዜ በአፍንጫ ወይም በጉንጭ አካባቢ ወይም በአፍ ውስጥ ይታያሉ።
· ፈሳሽ ማዠትና በላዩ ላይ የደረቀ ነገር መታየት፦ ትናንሽ ዉሃ የቋጠሩ እብጠቶች አንድ ላይ ይጣመሩና ይፈነዳሉ። ይህ ክፍተት ያለዉ፣ የሚያዥና በላዩ ላይ የደረቀ ነገር እንዲታይ ያደርጋል።
ምች ለመጀመሪያ ጊዜ ሲከሰት ከላይ ከተገለፁት ምልክቶች በተጨማሪ የሚከተሉትም በተጨማሪ ሊታዩ ይችላሉ፦
· ትኩሳት
· የድድ ህመም
· የጉሮሮ ህመም
· የራስ ምታት
· የጡንቻ ላይ ህመም
· አንገት አካባቢ እበጦች ናቸዉ።
ከአምስት አመት በታች ባሉ ልጆች ላይ ቁስሉ በአፋቸዉ ዉስጥ ሊወጣ ይችላል።
የህክምና ባልሙያዎምን ማማከር ያላብዎ መቼ ነዉ?
· የበሽታ መከላከል አቅምዎ ደካማ ከሆነ
· ህመሙ በ2 ሳምንታት ዉስጥ ካልዳነ
· የህመም ምልክቶቹ ከፍተኛ ከሆኑ
· ምች በተደጋጋሚ የሚከሰት ከሆነ
· አይንዎ ዉስጥ በተጨማሪ መቆጥቆጥ ካለዎ ናቸዉ።