ክፍል ሁለት
ሁሉም ሰዉ በሚባል ደረጃ ለምች የተጋለጠ ነዉ። ምንም እንኳን ምልክቶች ባይታዩም አብዛኛዎቹ ጎልማሶች ምች የሚያመጣውን ቫይረስ ተሸካሚ ናቸዉ። ቫይረሱ አንዴ ወደ ሰዉነትዎ ከገባ የተወሰኑ ምክንያቶች ቫይረሱ ምች እንዲያመጣ ሊቀሰቅሱት ይችላሉ። ምች ህመም እንዲቀሰቀስ ከሚያደርጉ ነገሮች ዉስጥ
· ኢንፌክሽን፣ የሰዉነት ትኩሳት፣ ጉንፋን ሲኖርዎ
· ለፀሃይ ብርሃን መጋለጥ
· ጭንቀት
· የበሽታ መከላከል አቅም መቀነስ፦ ኤች አይቪን ጨምሮ ሌሎች ህመሞች
· የወር አበባ ዑደት
· የቆዳ አለርጂ
· የካንሰር ህክምናዎች( ኬሞ ቴራፒ)
· የጥርስ ህክምናዎች ናቸዉ።
አንደገና በምች መታመም( Reinfection)
አንድ ሰዉ ምች ከያዘዉ በኃላ ማከም ይቻላል፤ ነገር ግን ከቫይረሱ ጨርሶ ማዳን አይቻልም። ቁስሉ ከዳነ በኃላ ቫይረሱ በሰዉነትዎ ዉስጥ ተደብቆ( remains dormant) ይቆያል። ይህ ማለት ቫይረሱ እንደገና ሲነቃቃ በማንኛውም ጊዜ አዲስ ቁስሎች ሊታዩ ይችላሉ። የሰዉነት በሽታ መከላከል አቅም አነስተኛ ከሆነ ምች በተደጋጋሚ ሊይዝዎ ይችላል።
መከላከል
በዓመት ከዘጠኝ ጊዜ በላይ የምች ቁስሎች ከታዩ ወይም ለከባድ ችግሮች የሚያጋልጥዎ ከሆነ ሐኪምዎ የፀረ-ቫይረስ መድሃኒት እንዲወስዱ ሊያዝልዎ ይችላል.
የጸሀይ ብርሀን በተደጋጋሚነት የሚቀሰቅስብዎ ከሆነ፣ ቁስሉ የሚፈነዳበት ቦታ ላይ የፀሐይ መከላከያ ክሬም ይጠቀሙ። ምች ወደ ሌሎች ሰዎች ወይም ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎችዎ እንዳይዛመት ለማገዝ፣ ከሚከተሉት የጥንቃቄ እርምጃዎች ውስጥ ጥቂቶቹን መሞከር ይችላሉ።
· ዉሃ የቋጠሩ ነገሮች በሚታዩበት ጊዜ ከሰዎች ጋር ከመሳሳምና የቆዳ ለቆዳ ንኪኪዎችን ያስወግዱ፦ ምች ዉሃ በሚቋጥሩበት ጊዜ ቫይረሱ በቀላሉ ይተላለፋል ወይም ይዛመታል።
· ዕቃዎችን በጋራ አለመጠቀም፦ የመመገቢያ እቃዎች፣ ፎጣዎች ፣ ከንፈር የሚቀቡ ነገሮችንና ሌሎች የግል እቃዎች ዉሃ የቋጠሩ ቁስል በሚታዩበት ጊዜ በጋራ መጠቀም ቫይረሱን ሊያሰራጩ ይችላሉ።
· የእጅ ንፅህናዎን ይጠብቁ፦ ምች ሲይዝዋ ሌሎች ሰዎችን በተለይም ህፃናትን ከመንካትዎ በፊት እጅዎን ይታጠቡ።
የምችል ህክምና
ምችን ሙሉ በሙሉ ማዳን አይቻልም። ነገር ግን ለማከም የሚረዱ ነገሮች
· የሚቀቡ ቅባቶችና ክሬሞች፦ ህመምን መቆጣጠርና ቁስሉን ለማዳን የሚረዱ እንደ ፔንሲክሎቪር (ዴናቪር) ባሉ ፀረ-ቫይረስ ቅባቶች መጠቀም ይችላሉ።
· መድሃኒቶች፦ ምች በአፍ የሚወሰድ እንደ አሳይክሎቪር ያሉ የፀረ-ቫይረስ መድሐኒት መዉሰድ
· የቤት ዉስጥ ህክምና፦ በቁስሎቹ ላይ በረዶ ወይም በቀዝቃዛ ውሃ የተነከሩ ጨርቆችን በመያዝ የህመም ምልክቶቹ ሊቀንሱ ይችላሉ።ቫዚሊን መቀባት ህመሙን ባይቀንሰዉም የቁስል መሰነጣጠቅ ይቀንሳል፣መቆጥቆጥንም ይቀንሳል።