094 046 4646/0940 565656    
info@sainturaelclinic.com
Follow Us:

View Blog

የጉልበት ላይ ህመም

የጉልበት ህመም በሁሉም ዕድሜ ክልል ላይ ያሉ ሰዎችን ሊያጠቃ የሚችል የተለመደ ህመም ነው። የጉልበት ላይ ህመም በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ሊከሰት የሚችል ሲሆን ከነዚህም ዉስጥ በአደጋ፣ እንደ አርትራይትስ ሪህና ኢንፌክሽን የመሳሰሉ ህመም ምክንያቶች ሊሆን ይችላል።
የህመም ምልክቶች
·       እብጠትና የጉልበት አልታዘዝ ማለት ወይም መጠንከር
·       ጉልበት ሲነካ የመሞቅና የመቅላት ስሜት መኖር
·       የጉልበት መስነፍ
·       የመንቋቋት ስሜት
·       ጉልበትዎን ሙሉ በሙሉ ለመዘርጋት መቸገር
የህክምና ባለሙያዎን ማማከር ያልበዎ መቼ ነዉ?
·       ጉልበትዎ ክብደት መሸከም አለመቻል ወይም ጉልበትዎ የተረጋጋ ካልመሰለዎ
·       ጉልበትዎ ላይ የጎላ እብጠት ምልክት መኖር።
·       ጉልበቶን ሙሉ በሙሉ መዘርጋት ወይም ማጠፍ ካዳገተዎ
·       በእግርዎ ወይም በጉልበቶ ላይ ግልጽ የሆነ የአካል ጉድለት ሲመለከቱ
·       ከጉዳት ጋር የተያያዘ ከባድ የጉልበት ህመም መኖር
አጋላጭ ምክንያቶች
በጉልበት ችግር የመጋለጥ እድሎትን ሊጨምሩ የሚችሉ በርካታ ምክንያቶች አሉ፡፡ ከነዚህም መካከል
·       ከመጠን ያለፈ ክብደት፦ ከመጠን በላይ ክብደት ወይም መወፈር በጉልበት መገጣጠሚያዎ ላይ መጨናነቅ ይጨምራል (እንደ መራመድ ወይም ደረጃ መውጣትና መውረድ ባሉ ተራ እንቅስቃሴዎች ላይም እንኳ።)
·       የጡንቻዎች መተጣጠፍና ጥንካሬ አለመኖር፦ የጥንካሬና የመተጣጠፍ ችሎታ ማጣት የጉልበት ጉዳቶችን ይጨምራል። ጠንካራ ጡንቻዎች መገጣጠሚያዎችዎን ለማረጋጋትና ለመጠበቅ ይረዳሉ።
·       የተወሰኑ ስፖርቶችና ስራዎች፦ አንዳንድ ስፖርቶች ከሌሎች ይልቅ በጉልበትዎ ላይ ከፍተኛ ጭንቀት ይፈጥራሉ።
·       የቀድሞ ጉልባት ላይ የደረሰ ጉዳት፦ ቀደም ሲል የጉልበት ጉዳት መኖሩ ጉልበቱን እንደገና የመጉዳት እድሉ ከፍተኛ ያደርገዋል።

Share with: