ክፍል አንድ
የጥፍር ፈንገስ ኢንፌክሽን በብዛት ከሚከሰቱትና ከተለመዱት የጥፍር ላይ ኢንፌክሽኖች አንዱ ነዉ። ህመሙ ሲጀምር በእግር ወይም እጅ ጣትት ጥፍርዎ ጫፍ ስር እንደ ነጭ ወይም ቢጫ-ቡናማ ነገር ይታያል ወይም ይጀምራል። የጥፍር ፈንገስ ብዙ የጣት ጥፍሮችን ሊያጠቃ ይችላል።
የጥፍር ፈንገስ በተለያዩ የፈንገስ አምጭ ተዋሲያን የሚከሰት ሲሆን በብዛት እንዲከሰት የሚያደርገዉ ደርማቶፋይት በሚባሉ የፈንገስ አይነቶች ነዉ።
የእግር ፈንገስ ወይም አትሌትስ ፉት( ጮቅ) ወደ እግር ጥፍሮች በመዛመት የጥፍር ፈንገስ ሊያመጣ ይችላል። በተመሳሳይ መልኩ የጥፍር ፈንገስ ወደ እግር በመዛመት የእግር ፈንገስ ሊያመጣ ይችላል። ፈንገስን ከጂም ሻወር ታይልስ፣ በላብ ምክንያትም ይሁን በሌላ ምክንያት እርጥበት የሚያጠቃቸዉ መጫሚያዎች ላይ በብዛት ይከሰታል።
የህመም ምልክቶች
የጥፍር ፈንገስ ምልክቶች ዉስጥ የጥፍር፦
· መወፈር
· ቀለም መቀየር
· በቀላሉ መሰባበር ወይም መፈርፈር፣ ችፍችፍ ማለት
· የቅርፅ መቀየር
· መነቀል
· ሽታ ማምጣት ናቸዉ።
አጋላጭ ነገሮች
ለጥፍር ፈንገስ ተጋላጭነትን ሊጨምሩ ከሚችሉ ነገሮች ዉስጥ
· በእድሜ መግፋት(እርጅና)
· እግርዎን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያልብዎ የሚያደርጉ ጫማዎችን ማድረግ
· ከዚህ በፊት የእግር ፈንገስ( ጮቅ) ኖሮቦት ከነበረ
· እንደ መዋኛ ገንዳዎች፣ ጂምና ሻወር ክፍሎች ባሉ እርጥብ በሆኑ የህዝብ መገልገያ ቦታዎች በባዶ እግር መራመድ
· ትንሽ የቆዳ ወይም የጥፍር ላይ ጉዳት መኖር
· እንደ ሶሪያሲስ ያሉ ጥፍርንም ሊያጠቁ የሚችሉ የቆዳ ችግሮች መኖር
· የስኳር በሽታ፣ የደም ፍሰት ችግር ወይም የበሽታ መከላከል አቅም ማነስ ካልዎ ናቸዉ።