የጎንዮሽ ጉዳት
ከባድ የጥፍር ፈንገስ የጥፍር ህመምና በጥፍርዎ ላይ ዘላቂ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል። በመድሃኒት፣ በስኳር በሽታ ወይም በሌሎች ሁኔታዎች የበሽታ መከላከል አቅምዎ የተዳከመ ከሆነ የፈንገስ ኢንፌክሽኑ ከጥፍርና እግርዎ አልፎ ወደ ሌሎች የሰዉነትዎ ክፍል እንዲሰራጭ ሊያደርግ ይችላል።
መከላከል
የሚከተሉት ልማዶች የጥፍር ፈንገስ ወይም ሪኢንፌክሽን እና የአትሌት እግርን ለመከላከል ይረዳሉ፣ ይህም ወደ ጥፍር ፈንገስ ይመራል።
· ጥፍርዎን ንጹህና ደረቅ ያድርጉ ፦ እጅዎንና እግርዎን በየጊዜው ይታጠቡ፣ኢንፌክሽን የፈጠረ ጥፍር ከነኩ በኋላ እጅዎን በአግባቡ ይታጠቡ። ከታጠቡ በኃላ በደንብ ያደራርቁት።
· ጥፍርዎን በአግባቡ ይቁረጡ፡- ጥፍርዎን ከቆረጡ በኃላ መቁረጫዉን በደንብ ያፅዱት፣ ጥፍርዎ እንዲረዝም መፍቀድ ፈንገስ እንዲያድግ ወይም እንዲስፋፋ ተጨማሪ ቦታዎችን መፍተር ማለት ነዉ።
· ላብ የሚመጡ ካልሲዎችን ያድርጉ እንዲሁም ካልሲዎትን ይቀያይሩ
· በመዋኛ ቦታዎች፣ ጂም ሻወር ቤትና እርጥበታማ ቦታዎች ሲሄዱ ጫማ ያድርጉ።
· ለእያንዳንዱ ደንበኛ ስቴራላይዘር ማሽን (sterilized manicure) መሳሪያዎችን የሚጠቀም የጥፍር ሳሎን ይምረጡ።
· የጥፍር ቀለምና አርቲፊሻል ጥፍር ከመጠቀም ይቆጠቡ።
· የእግር ፈንገስ ( ጮቅ) ካለዎ በጊዜ ይታከሙ።