094 046 4646/0940 565656    
info@sainturaelclinic.com
Follow Us:

View Blog

የምግብ ያለመፈጨት ችግር

መንስኤ
የምግብ ያለመፈጨት ችግር ብዙ መንስኤዎች አሉት። ብዙ ጊዜ የምግብ አለመፈጨት ችግር ከአኗኗር ዘይቤ ጋር የተያያዘ ሲሆን በምግብ፣ በመጠጥ ወይም በመድሃኒት ሊነሳ ይችላል። የተለመዱ የምግብ አለመፈጨት መንስኤዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ:-
·       ከመጠን በላይ መብላት ወይም በፍጥነት መብላት
·       ቅባትና ቅመም የበዛባቸው ምግቦች
·       ከመተን ያለፈ ወይም በጣም ብዙ ካፌይን፣ አልኮል፣ ቸኮሌት ወይም ለስላሳ መጠጦች
·       ሲጋራ ማጨስ
·       ጭንቀት
·       የተወሰኑ ፀረ-ባክቴሪያና ህመም ማስታገሻዎች
ለምግብ ያለመፈጨት ችግር ሊደረጉ የሚችሉ ህክምናዎች
የአኗኗር ዘይቤ ለዉጥ ማድረግ የምግብ ያለመፈቸት ችግርን ሊቀንስ ይችላል። በተጨማሪም
·       የምግብ ያለመፈጨት ችግርን ሊያባብሱ የሚችሉ ምግቦችን ከመመገብ መቆጠብ
·       በቀን ዉስጥ አብዝቶ ሶስቴ ከመመገብ ይልቅ መክሰሶችን ጨምሮ በቀን አምስት ወይም ስድስት ጊዜ በትንሽ በትንሹ አድርጎ መመገብ
·       የአልኮሆል መጠጥንና የካፌይን አጠቃቀምን መቀነስ ወይም ማስወገድ
·       የተወሰኑ እንደ አስፕሪን፣ ጎፈን ወይም አድቪል፣ ዳይክሎፌናክና የመሳሰሉ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶችን ከመዉሰድ መቆጠብ
·       ጭንቀትን መቀነስ ወይም ማስወገድና
ከላይ የተጠቀሱትን ተግብረዉ የምግብ አለመፈጨት ችግርዎ ከቀጠለ መድሃኒቶች መዉሰድ ያስፈልጋል። በመጀመሪያ ያለሃኪም ትዕዛዝ ሊወሰዱ የሚችሉ ሽሮፖችንና ሊሎች በእንክብል መልክ ያሉ አንቲ አሲዶችን መጠቀም ይችላሉ። በዚህም መሻሻል ከሌለዉ የህክምና ባልሙያዎን ያማክሩ።
የምግብ ያለመፈጨት ችግር በቤት ዉስጥ ሊደረግ የሚችል ህክምና
መጠነኛ የምግብ ያለመፈጨት ችግር ላላቸዉ ሰዎች ሊደረግ የሚችል የቤት ዉስጥ ህክምና
·       ትንሽ፣ ትንሽ ብዙ ጊዜ ወይም በተደጋጋሚ ምግቦችን መመገብ
·       ቀስቃሽ ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን ማስወገድ፦ ቅባትና ቅመም የበዛባቸው ምግቦች፣ በፋብሪካ የተቀነባበሩ ምግቦች፣ ካርቦኔትድ መጠጦች፣ ካፌይን፣ አልኮልና ሲጋራ ማጨስ የምግብ አለመፈጨት ችግርን ሊያስከትሉ ይችላሉ።
·       የተመጣጠነ የሰዉነት ክብደት እንዲኖርዎ ማድረግ፦ ከመጠን በላይ የሰዉነት ክብደት በሆድዎ ላይ ጫና ስለሚፈጥር ጨጓራዎን ወደ ላይ በመግፋት አሲድ ወደ ምግብ ቧንቧዎ እንዲመለስ ያደርጋል
·       በመደበኛነት የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ማድረግ፦ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ክብደትን ላመቀነስ ስለሚረዳ የምግብ መፈጨትን ያግዛል።
·       ጭንቀትን ማስወገድ፦
·       ጨጓራው እንዲቆጣ የሚያደርጉ መድሃኒቶችን ማስወገድ ናቸዉ።

Share with: